የአ.አ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጥሪ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ መጪው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ነዋሪዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
ለወንጀል መከላከል፣ መቆጣጠርና ሰላማዊ የምርጫ ሂደት የህዝቡ ሚና በሚል ውይይት ያካሄደው ቢሮው ለፀጥታና ለደኅንነት ሥራ ትልቁ አቅም ሕዝብ መሆኑን በመጥቀስ ህዝቡ በየአካባቢው ያለውን የፀጥታ ሁኔታን በትኩረት በመከታተልና የወንጀል ድርጊት ሲያጋጥም ለፀጥታ አካል መረጃ በማድረስ የከተማን ሰላም ለማረጋገጥ እንዲሰራም ጠይቋል፡፡
ምርጫውን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የወንጀል ድርጊቶችን ቀድሞ በመከላከል እንዲሁም ለፀጥታ መዋቅሩ ጥቆማ በመስጠት ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲያልፍ ማህበረሰቡ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት እንዲወጣም ቢሮው አሳስቧል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
