የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችና የነዳጅ ቀውስ
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መኖራቸው አሁንም ድረስ ለቀጠለው የነዳጅ ዋጋ መዋዠቅ እንደ መከላከያ ሆኖ ማገልገሉን ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊት በነዳጅና በናፍጣ የሚሰሩ ተሸከርካራችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በመከልከሏ አሁን ላይ በሀገሪቱ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከ100 ሺህ በላይ መድረሱ ተነግሯል፡፡
እንደ አሶሺየትድ ፕሬስ ዘገባ ከሆነ፣ ይህ ውሳኔ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ እጥረት፣ በማደያዎች የሚስተዋሉ ረጅም ሰልፎችንና የነዳጅ ዋጋ ንረትን ለማስቀረት አዎንታዊ አስተወጽኦ አድርጓል፡፡
ያሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት አፍሪካ ከቻይና ከ44 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ያስመጣች ሲሆን ይህም በ2024 ከነበረው ወደ 19ሺህ ገደማ ከሚሆነው ቁጥር ከእጥፍ በላይ ብልጫ እንደላውና በኢትዮጵያ ካሉ አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የ8 በመቶ ድርሻ እንደሚይዙ ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን በየዓመቱ ለነዳጅ ገቢ ምርት ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደምታወጣ የተነገረ ሲሆን ከኢራን ጦርነት ጋር የተያያዙት ዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎሎች ጋዝና ናፍጣን ይበልጥ ማግኘት አስቸጋሪ አድርገውታል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
