የተነሳው ገደብ
የብሔራዊ ባንክ ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲካሄድ ጥሎት የነበረውን ገደብ አነሳ።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ እና በቻይና መንግስት ስምምነት መሰረት ወደ ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲሰጥ ተወስኖ እንደነበር አስታውሷል።
ባንኩ የወጪ ንግድ ዘርፉን ለማቀላጠፍ ፣ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እና ለላኪዎች ምቹና ተደራሽ የባንክ አገልግሎት ለመፍጠር ሲባል ገደቡ ተነስቷል ብሏል።
ባንኩ ከዛሬ ግንቦት 18 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ የባንክ አገልግሎቶች በሁሉም ባንኮች በኩል እንዲሰጥ ፈቅዷል።
የንግድ ባንኮች ከተለመዱት የወጪ ንግድ እና የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች በተጣጣመ መልኩ አገልግሎቱን ለደንበኞቹ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ብሔራዊ ባንክ አሳስቧል።
መረጃው ከብሔራዊ ባንክ የተገኘ ነው
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
