EthiopiaNews

የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ

ሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በማፅደቅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት መምራቱን አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ይሄን ያለው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ባሳለፈበት መግለጫ ላይ ነው።

ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም የነበረውን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ላይ በርካታ ማሻሻያ ተደርጎ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ገልጿል።

ረቂቅ አዋጁ የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ከዘመናዊ ዓለም አቀፍ ልምዶች ጋር ለማጣጣም፤ የታክስ አለመግባባቶችን በፍትሐዊነት፣ በሰላማዊ መንገድና በቅልጥፍና ለመፍታት በሚያስችል መልኩ ተዘጋጅቷል ተብሏል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ መረጃው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv