EthiopiaNews

ስራ የጀመሩት የምርጫ ታዛቢዎች

የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች ምርጫውን ለመታዘብ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ሥራ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት የአፍሪካ ሕብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ተወካዮቻቸውን ልከው ምርጫውን የመታዘብ ሥራቸውን ጀምረዋል።

ከሁለቱ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተጨማሪ በሀገር ውስጥ የተደራጁ 55 ሲቪክ ማኅበራትም ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ መግባታቸውን ሰብሳቢዋ አስታውሰዋል።

55ቱ የሀገር ውስጥ ታዛቢ ተቋማቱ 1 ሺህ 562 የምርጫ ታዛቢዎችን ማሰማራታቸውንም ነው ሰብሳቢዋ አክለው የጠቀሱት።

59 አባላት ያሉት የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ደግሞ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ እየተመራ ሥራውን እንደሚሠራም አስታውቀዋል።

ኢጋድ በበኩሉ 26 አባላት ያሉት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን እንደሚያሰማራ ነው የጠቀሱት።

በአዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶችም የምርጫውን ሂደት ተዘዋውረው እንዲመለከቱ የእንግድነት ማለፊያ እንደተሰጣቸው ሰብሳቢዋ ተናግረዋል።

#EBS

#EBSTVNEWS

#EBSTVSPORT

#_7696_WN

https://t.me/ebstvnews

www.ebstv.tv