EthiopiaNews

በድሬዳዋ የምርጫ ቁሳቁሶች ስርጭት 

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የሚያገለግሉ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጩ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዚያድ ያሲን መሀመድ ገልፀዋል።

በነገው ዕለት ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለድምፅ አሰጣጡ የተሟላ ዝግጅት እየተደረገ ነው የተባለ ሲሆን በዚህም መሰረት የምርጫ ቁሳቁሶች ከትናንት ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

ቁሳቁሶቹ በአስተማማኝ ሁኔታ ወደ የጣቢያዎቹ እንዲደርሱም በአስተዳደሩ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተመደቡ የፀጥታ ኃይሎች ሂደቱን እያጀቡ እንደሚገኙም ተነግሯል።

በአስተዳደሩ ስር የሚገኙ 297ቱም የምርጫ ጣቢያዎች የድንኳን ተከላ እና የአዳራሽ ዝግጅቶች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው ሲገለፅ በትናንትናው ዕለት ደግሞ በአራቱም የገጠር ክላስተሮች ሥር ለሚገኙ 130 የምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ ስርጭት ቀድሞ መከናወኑ ተጠቁሟል።

የቁሳቁስ ስርጭቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ በየምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽ ይሆናሉም ተብሏል።

#EBS

#EBSTVNEWS

#EBSTVSPORT

#_7696_WN

https://t.me/ebstvnews

www.ebstv.tv