የድምጽ መስጫ ሰአት መራዘም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምሽት 12 ሰዓት ይጠናቀቅ የነበረውን የድምጽ መስጪያ ጊዜ ማራዘሙን አስታወቀ፡፡
የተራዘመው ጊዜ የሚቆየው እስከ 12 ሰዓት ድረስ ሰልፍ ላይ የነበረው መራጭ ድምጽ ሰጥቶ እስኪያጠናቀቅ መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል።
ቦርዱ ይሄንን ውሳኔ የወሰነው በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ መሰረት በልዩ ሁኔታ የድምፅ መስጫ ሰዓት ሊራዘም እንደሚችል መደንገጉን ተከትሎ ነው፡፡
#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
