InternationalNews

በአሜሪካና ኢራን መካከል የተደረሰውን የመርህ ስምምነት ተከትሎ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ሲያሳይ የአክሲዮን ገበያዎች ዋጋ ደግሞ አንሰራርቷል።

በተለይም የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ያሳየው ለዓለም ገበያ ከሚቀርበው ነዳጅ 20 ከመቶ የሚሆነው የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ በስምምነቱ መሰረት የሚከፈት በመሆኑ ነው፡፡

አሁን ብረንት የተባለው ነዳጅ ዋጋ በ4 ነጥብ 7 ከመቶ ቀንሶ አንዱ በርሜል በ83 ዶላር ከ24 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን የአውሮፓና እስያ የአክሲዮን ገበያም ማንሰራራት ጀምሯል፡፡

ይሁንና በፓኪስታን ሽምግልና የተካሄደውና በቅርቡ በስዊዘርላንድ ይፈረማል ተብሎ የሚጠበቀው የሰላም ስምምነት ዝርዝር ጉዳይ የያዘ ባለመሆኑ የመጽናቱ ጉዳይ በጥርጣሬ እየታየ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv