የአሜሪካ ኤምባሲ በፈረንጆቹ 2027 /28 አመት ለሚሰጠው የሁበርት ኤች ሃምፍሬይ የስልጠና መርሃግብር ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ።
ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ የስልጠና እና የልምምድ ልውውጥ ኘሮግራሙ በአሜሪካ መንግሥት ሙሉ ወጪው የሚሸፈን መሆኑን ገልጾ እድሜያቸው ከ32 እስከ 45 ያሉ ኢትዮጵያውያን አመልካቾች በስልጠናው ለመሳተፍ ማመልከት እንደሚችሉ አሳውቋል።
ይሄው መርሃ ግብር ባለሙያዎች ብቃታቸውን የሚያሳድጉበትና ከአሜሪካውያን አቻዎቻቸው ጋር ጠንካራ የሥራ ትስስር የሚፈጥሩበት ልዩ መድረክ እንደሆነ ተገልጿል።
ፍላጎቱ ያላቸው ኢትዮጵያውያን አመልካቾች እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በበይነ መረብ ብቻ ማመልከት እንደሚችሉ ኤምባሲው ገልጿል። መረጃው ከአሜሪካ ኤምባሲ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
