InternationalNews

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በኢራን ጦርነት ወቅት ገለልተኛ መሆን በመቻላቸው ምስጋና አቀረቡላቸው።

ትራምፕ ይህንን ምስጋና ያቀረቡት ለቡድን 7 አባል ሀገራት ጉባኤ ከሚገኙበት ፈረንሳይ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች አሜሪካ ኢራን የኒውክለር ጦር መሳሪያ እንዳይኖራት እየወሰደች ያለችውን እርምጃም ለማደናቀፍ አልሞከሩም ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የቻይናና ሩሲያ መሪዎች የኢራን ጦርነት ለእኛ እንዲከብድ ማድረግ ይችሉ የነበረ ቢሆንም በጦርነቱ ጣልቃ ከመግባት ተቆጥበናል ብለዋል።

ሩሲያና ቻይና ለኢራን ከመሬት ወደ አየር የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችንና ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን በመላክ አሜሪካን ዋጋ ማስከፈል ይችሉ ነበር ያሉት ትራምፕ ይህንን ባለማድረጋቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv