EthiopiaNews

በኢትዮጵያ በ11 ወራት ከ3.1 ሚሊዮን በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦንላይን ተሰጠ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በ11 ወራት ከ3.1 ሚሊዮን በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦንላይን መሰጠቱን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ 3,090,810 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት አቅዶ ከ3.1 ሚሊየን በላይ አገልግሎቶችን በመስጠት የእቅዱን ከመቶ በመቶ በላይ ተሳክቷል ብሏል።

ሚኒስቴሩ ይህ የአፈጻጸም ደረጃ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ11 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ይሄ አፈፃፀም እንዲመዘገብ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተዘረጋው የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ሥርዓት የጎላ ሚና ተጫውቷል ብሏል። መረጃው ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv