EBS SPORT – እለታዊ መረጃዎች

  • ኢትዮጵያ እና ግብፅ በአፍሪካ ዋንጫው በሚያደርጉት ጨዋታ 3 የፈርኦኖቹ ኮከቦች በጉዳት ምክንያት ከስብስብ ውጭ መሆናቸው ተገልፅዋል፡፡ የፊታችን ሀሙስ ምሽት በቢንጉ በሚደረገው ፍልምያ የሊቨርፑሉን ኮከብ መሀመድ ሳላህን ጨምሮ ግብ ጠባቂው ኤል ሼናዊ እና አጥቂው መሀመድ አህመድ ትሬዝጌት በግብጽ በኩል ከጨዋታው ውጭ ሆነዋል፡፡
  • 54 ሀገራት የሚካፈሉበት የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን ረቡዕ በሞሪሺየስ አስተናጋጀትነት ሲጀመር ኢትዮጵያ በመድረኩ ለ22ኛ ጊዚ ተሳታፊ ትሆናለች፡፡ ከ1979 አንስቶ በሁሉም የአትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ላይ መሳተፍ የቻለችው ኢትዮጵያም በሴንት ፔይሬው የአትሌቲክስ ድግስ ላይ በ7 የውድድር ዘርፎች በ54 ስፖርተኞች የምትወከል ይሆናል፡፡
  • በ5ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው ሴካፋ ሀገራት የእግር ኳስ ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ የሆኑት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አባላት በግማሽ ፍጻሜው የኡጋንዳ አቻቸውን ያገኛሉ፡፡ ምድባቸውን በ7 ነጥቦች በሁለተኛነት ያጠናቀቁት ሉሲዎቹ የውድድሩን አስተናጋጅ ዩጋንዳን የፊታችን ሀሙስ በ7፡00 በኒጂሩ ስቴዲየም የሚገጥሙ ይሆናል፡፡   
  • የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የፊታችን ሀሙስ ከግብፅ አቻው ጋር ላለበት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅቱን ቢሾፕ ማኬንዚ ማድረጉን ቀጥሏል፡፡ በማላዊ ከከተመ ዛሬ 5ኛ ቀኑን ያስቆጠረው ቡድኑ ለወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በቀን አንድ ጊዚ ልምምዱን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመራ እያደረገ ይገኛል፡፡
  • ሱራፌል ዳኛቸው እና ያሬድ ባየህ በፊታችን ሀሙሱ ጨዋታ በጉዳት ምክንያት የመሰለፍ እድላቸው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡ ሁለቱ ተጫዋቾች ባሳለፍነው እሁድ ጉዳት የገጠማቸው ሲሆን ከቡድኑ ጋር ግን ሙሉ ልምምድ ሳያደርጉ ቀርተዋል፡፡ በዚህም በግብፁ ጨዋታ ላይ ያሬድ ባየህ እና ሱራፌል ዳኛቸው በቋሚ አሰላለፍ ላይካተቱ ይችላሉ፡፡
  • ማንችስተር ዩናይትድ የዴንማርካዊው አማካይ ክርስትያን ኤሪክሰን ፈላጊ ሆኖ ቀርቧል፡፡ በያዝነው ወር ኮንትራቱን ከብሬንትፎርድ ጋር የሚያገባድደው አማካይ  ከልብ ህመም መልስ ዳግም ወደ ሜዳ ተመልሶ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል፡፡ በዚህም ተጫዋቹን በነጻ ለማዛወር ዩናይትዶች ከወዲሁ እንቅስቃሴዎች ጀምረዋል፡፡
  • አርጀንቲናዊው የመስመር አማካይ አንሄል ዲማሪያ በነጻ ዝውውር የስፔኑን ክለብ ባርሴሎናን ሊቀላቀል ከጫፍ ደርሷል፡፡ ኮንትራቱን ከፓሪሴንት ጀርሜን ጋር ያጠናቀቀው ተጫዋቹ በጁቬንቱስ በጥብቅ ቢፈለግም በመጨረሻም ግን ወደ ብላግናራዎቹ አምርቶ ለባርሴሎና ለመጫወት ከስምምነት መድረሱ ከወደ ስፔን ተሰምቷል፡፡
  • የማንችስተር ሲቲውን የፊት መስመር ተጫዋች ጋብሬል ጀሱስን  ለማዛወር 4 ክለቦች ተፋጠዋል፡፡ የኤርሊንግ ብራውት ሃላንድን ወደ ኢትሃድ ማቅናት ተከትሎ ውሃ ሰማያዊዎቹን እንደሚለቅ የሚጠበቀውን ብራዚላዊ ለማግኘት አርሰናል ሪያል ማድሪድ እንዲሁም ቶትንሃም እና ቼልሲ ጥልቅ ፍላጎት ማሳየታቸውን ማርካ አስነብቧል፡፡  
  • በአውሮፓ ሀገራት ሊግ ሰኞ ምሽት በተደረጉ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ፈረንሳይ ነጥብ ስጥትል ዴንማርክ በአሸናፊነት ጉዞዋ ቀጥላለች፡፡ ወደ ፖሊውድ አቅንታ ክሮሺያን የገጠመችው ፈረንሳይ ከክሮሺያ 1 አቻ ተለያይታለች፡፡ በኄርኔት ሃፕል ስታዲዮን ዴንማክን ያስሰተናገደችው ኦስትሪያም የ2-1 ሽንፈት ገጥሞቷል፡፡
  • የአውሮፓ ሀገራት ሊግ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ረቡዕ ምሽት በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡፡ 55 ሀገራት በተለያዩ 4 የሊግ  እረከኖች የሚሳተፉበት ሻምፒዮናም ነገ ምሽት 3፡45 ያልተጠበቀ ሽንፈት በሆላንድ የገጠማት ቤልጂየም ከፖላንድ  ትጫወታለች፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት ወደ አለም ዋንጫ ያቀናችው ዌልስ ኔዘርላንድን በካርዲፍ ትገጠማች፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New