NewsSports

EBS SPORT – የብራዚሉ የእግር ኳስ ኮኮብ ፔሌ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

ከካንሰር ህመም ጋር ሲታገል የቆየው የእግር ኳሱ ንጉስ ኤድሰን አራንቴስ ዶናሴሜንቶ(ፔሌ) 👑 በመጨረሻም እጁን ሰጥቷል፡፡ ሶስት የአለም ዋንጫዎችን በማሸነፍ ብቸኛ የሆነው ይህ ህያው ተጫዋች ከአንጀት ካንሰር ጋር በተያያዝ በተደጋጋሚ ወደ አልበርት አንስታይን ሆስፒታል ሲገባ እንደነበር እና ከቀናት በፊት ቤተሰቦቹን መሰናበቱ የሚታወቅ ሲሆን በትላንትናው ዕለትም በ82 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፡፡ህልፈቱን ተከትሎም ሮናልዶ ሊውስ ናዛሪዮ ዴሊማ፣ኔይማር ጁኒየር፣ሊዮኔል ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶን ጨምሮ በርካታ የስፖርቱ አለም ፈርጦች እና ክለቦች ፔሌ ለእግር ኳሱ ላበረከተው ነገር ምስጋናቸውን በማቅረብ ሃዘናቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሰኞ ማለዳ ላይ የፔሌ አስከሬን ከአልበርት አንስታይን ሆስፒታል ወደ ቀድሞ ክለቡ ሳንቶስ ስታዲየም ቪላ ቤልሚሮ እንደሚወሰድ እና እስከ ማክሰኞ በሜዳው መሃል ላይ እንደሚቀመጥ ተገልጿል፡፡ ከዚያም የፔሌ የሬሳ ሣጥን በሳንቶስ ከተማ ጎዳናዎች እና የተጨዋቹ እናት የሆኑት የ100 አመቷ ሴሌስቴን አራንቴስ በሚኖሩበት በማለፍ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ እንደሚፈጸም እየተነገረ ይገኛል፡፡ ፔሌ በ2020 የማራዶናን ከዚህ አለም በሞት መለየት ተከትሎ አንድ ቀን ሰማይ ቤት በጋራ ኳስ እንደምንጫወት ተስፋ አደርጋለሁ ማለቱ አይዘነጋም፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New