News

አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

🇦🇫#አፍጋኒስታንየመንግስታቱ ድርጅት በአፍጋኒስታን የታሊባን አስተዳደር በሴቶች ላይ የጣለውን እገዳ እንዲያነሳ ጥሪውን አቀረበ።የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ታሊባን ሴቶች ዩኒቨርስቲ እንዳይገቡ እና በረድኤት ተቋሟት ተቀጥረው እንዳይሰሩ ያስተላለፈውን ገደብ በፅኑ አውግዞ ገደቦቹም እንዲነሱ ጠይቋል።የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው የታሊባን እገዳዎች የሴቶችን መብቶች የሚጥሱ በመሆናቸው በአስቸኳይ እንዲነሱ እንጠይቃለን ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

🇦🇫#ሩሲያበሩሲያ የነዳጅ ምርቶች የዋጋ ተመን ለጣሉ አገራት የነዳጅ ዘይት ሽያጭ እንዳይደረግ የሚያግድ ህግ ሩሲያ አፀደቀች።ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዋጋ ተመኑን ተፈፃሚ ለሚያደርጉ የምዕራባዊያን አገራት የነዳጅ ዘይት ሸያጭ እንዳይከናወን የሚከለክለውን ህግ በፊርማቸው አፅደቀዋል።የሩስያ አዲሱ ህግ በተለይ በአውሮፓ ህብረት ፣ በበለፀጉት የቡድን 7 አገራት እና አውስትራሊያ ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን አር ቲ ዘግቧል ።

🇮🇷#ኢራን በኢራን ከወራት በፊት ተቀስቅሶ በነበረው ህዝባዊ አመፅ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 476 መድረሱ ተነገረ ።መቀመጫውን ኖርዌይ ያደረገው የኢራን የሰብአዊ መብት ተቋም ባወጣው መረጃ 64 ታዳጊዎች እና 34 እናቶችን ጨምሮ በፀጥታ ሀይሎች የተገደሉ ዜጎች ቁጥር 476 ደርሷል ብሏል ።ምዕራባዊያን ኢራን በሰልፈኞች ላይ የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ፈጽማለች በሚል ሲከሱ የቴህራን መንግስት አገራቱ በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ እየገቡብኝ ነው ሲል ክሳቸውን ማጣጣሉን አናዶሉ ዘግቧል።

🇸🇸#ደቡብ ሱዳንበደቡብ ሱዳን በደረሰ የጎሳ ግጭት 56 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸው ተገለፀ።በደቡብ ሱዳን በምስራቃዊቷ የጆንጌሊ ግዛት ላለፉት 4 ቀናት ሲካሄድ በነበረው ግጭት ነው 56 ሰዎች መገደላቸው የተነገረው ።ግጭቱ በኑዌር እና የሙርሌ ጎሳ አባላት መካሄዱ ሲነገር ከአጠቃላይ ሟቶች 51ዱ ከኑዌር የተቀሩት 5ቱ ከሙርሌ ጎሳ መሆናቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New