News

አዲስ ነገር – የስልክ አገልግሎት በመቀሌ

ከ2 ዓመታት በኋላ ወደ ትናንት መቀሌ ከተማ የስልክ አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።በዚሁ ቀን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ የመጀመሪያውን ስልክ በመደወል አገልግሎቱ መጀመሩን አብስረዋል። በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የስልክ አገልግሎት ለማስጀመር 981 ኪሎ ሜትር የፋይበር ጥገና ተከናውኖ በ27 ከተሞች የስልክና ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ማስጀመር መቻሉንም ገልጸዋል።አገልግሎቱ ቢጀመርም ታዲያ ተገልጋዮች ላለፉት 2 አመታት ካርድ ባለመሙላታቸውና የቴሌ የሽያጭ ማእከላትም አገልግሎት ባለመጀመራቸው የተነሳ በመቀሌ ያሉ ተጠቃሚዎች ወደሚፈልጉት ቦታ ለመደወል ሊቸገሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።ለዚህ መፍትሄ ለማበጀትና የሽያጭ ማእከላትን መልሶ ለማደራጀት እየሰራ መሆኑን ያሳወቀው ኢትዮ ቴሌኮም እስከዛው ግን በመቀሌ ያሉ ተጠቃሚዎች ከሌሎች ቦታዎች የአየር ሰአት በማስላክ አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ ነው ብሏል።9 ቡድኖችን በ4 አቅጣጫ በማሰማራት አሁንም ስራ ላይ መሆኑን የጠቆመው ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌኮም አገልግሎቱ ዳግም መጀመር በመቻሉ 61 የባንክ ቅርንጫፎችም ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ እንደተቻለ አሳውቋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New