News

አዲስ ነገር – አጫጭር የውጭ መረጃዎች

🇺🇸#አሜሪካአሜሪካ ለዩክሬን 1.85 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ተጨማሪ የጦር መሣሪያዎች ድጋፍ ይፋ አደረገች።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በአሜሪካ ጉብኝት እያደረጉ ያሉትን የዩክሬኑን ፕሬዝንዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በዋይት ሀውስ ከተቀበሉ በኋላ ነው ለዩክሬን የ1.8 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ ያደረጉት።የባይደን አስተዳደር ለዩክሬን ያፀደቀው ድጋፍ “ፓትሮት” የተሰኘውን የአየር መቃወሚያ ስርአት የሚያካትት መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

🇷🇺#ሩሲያሩሲያ የተዋጊ ወታደሮቿን ቁጥር ወደ 1.5 ሚሊየን ልታሳድግ መሆኑ ተገለጸ።የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት “ኔቶ” በደቀነው ስጋት የተዋጊ ወታደሮች ቁጥር ወደ 1.5 ሚሊየን እንዲያድግ ወስኗል።ሚኒስቴሩ በሩሲያ የሰሜን ምዕራብ ድንበር ልዩ የጦር ሀይል የማስፈር እቅድ መያዙንም አር ቲ ዘግቧል።

🇨🇳#ቻይናየአለም የጤና ድርጅት በቻይና ያገረሸውን የኮሮና ወረርሽኝ ተከትሎ በአገሪቱ ያሉ የጤና ተቋሟት በህሙማን ሊጨናነቁ እንደሚችሉ ስጋቱን ገልጿል።የጤና ድርጅቱ የቴክኒክ ጉዳዮች ሀላፊ ዶ/ር ማይክል ራያን በቻይና ባገረሸው የኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ በከተሞች ያሉ የፅኑ ህሙማን ክፍሎች እየሞሉ መምጣታቸው ስጋት ፈጥሯል ብለዋል።የቻይና መንግስት ከ2 ሳምንታት በፊት የኮሮና ክልከላዎችን ማንሳቱን ተከትሎ የኮሮና ወረርሽኝ እየተስፋፋ መጥቷል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ።

🇸🇴#ሶማሊያ በኤርትራ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ የሶማሊያ ወታደሮች ወደ አገራቸው መመለስ መጀመራቸው ተነገረ።በኤርትራ ወታደራዊ ሰልጠና እየወሰዱ ካሉ ከ5 ሺ ከሚልቁት ወታደሮች ውስጥ ነው የተወሰኑት ወደ ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ መመለስ መጀመራቸው የተዘገበው ።ከኤርትራ የተመለሱት ወታደሮች የአሸባሪው አልሸባብን ለመዋጋት ወደ ግዳጅ በሚሰማሩበት ሁኔታ ላይ የታወቀ ነገር እንደሌለ ሲጂቲኤን ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New