News

አዲስ ነገር – የዓለም ውሎ

🇺🇦#ዩክሬን የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ዛሬ በአሜሪካ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የዩክሬን -ሩስያ ጦርነት ከጀመረ ከ 9 ወራት ወዲህ የመጀመሪያው በሆነው የአሜሪካ ጉብኝታቸው ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ተገናኝተው በዋይት ሐውስ ይመክራሉ ተብሏል።ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ዩክሬን ከዩናይትድ ስቴትስ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች እና ሌሎች ድጋፎች እንዲደረግላት በይፋ ይጠይቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ ዘግቧል ።

🇦🇫#አፍጋኒስታን በአፍጋኒስታን የታሊባን አስተዳደር ሴቶች ዩኒቨርስቲ እንዳይገቡ አዲስ እገዳ መጣሉ ተነገረ ።የአፍጋኒስታን የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በአገሪቱ ሴቶች ዩኒቨርስቲ እንዳይገቡ የተጣለው እገዳ በአስቸኳይ በመላ አገሪቱ ተፈፃሚ እንደሚሆን አስታውቋል።የመንግስታቱ ድርጅትን ጨምሮ በርካታ አገራት የታሊባን አስተዳደር ያወጣውን እገዳ እያወገዙ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

🇨🇩#ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ላይ ጥሎት የነበረውን የጦር መሣሪያ ግዥ ማዕቀብን አነሳ።የማዕቀቡ መነሳት የኪንሻሳ መንግስት ያለ አንዳች ገደብ የጦር መሣሪያዎች መግዛት እንዲችል ሲረዳው በምስራቃዊው ኮንጎ በሚንቀሳቀሰው “የኤም23” ታጣቂ ቡድን ላይ የሚወስደውን እርምጃ ያጠናክርለታል ተብሏል።የኪንሻሳ መንግስት የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ ከዚህ ቀደም የተፈፀሙ ስህተቶችን የሚያርም ምላሽ ነው ሲል ማድነቁን ዘኢስት አፍሪካን ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New