News

አዲስ ነገር – የዓለም ውሎ

🇷🇺#ሩስያ ቻይና እና ሩስያ ከ2 ቀናት በኋላ የተቀናጀ የባሕር ሀይል ልምምድ ሊያደርጉ መሆኑ ተዘገበ።የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ከ 2 ቀናት በኋላ በምስራቅ የቻይና ባሕር ላይ የሚካሄደው የቤጂንግ እና የሞስኮ የባሕር ሀይል ልምምድ የአገራቱን ወታደራዊ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው ብሏል ።ቻይና እና ሩሲያ ከአውሮፓውያኑ 2012 ጀምሮ በየአመቱ የባሕር ሀይል ወታደራዊ ልምምድ እያካሄዱ እንዳለ አናዶሉ ዘግቧል ።

🇪🇺#የአውሮፓ ህብረትየአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀት ለመቀነስ የሚረዳ አዲስ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነገረ ።የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባል አገራት በፈረንጆቹ 2030 የበካይ ጋዝ ልቀትን በ62 ከመቶ ለመቀነስ ከስምምነት መድረሳቸውን አስታውቋል ።የህብረቱ አባል አገራት የበካይ ጋዝ ልቀትን ከመቀነስ ባሻገር የታዳሽ ሀይል ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነትን ለማስፋፋት ከመግባባት መድረሳቸውን ፍራንስ ቱዌንቲ ፎር ዘግቧል።

🇿🇦#ደቡብ አፍሪካ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የገዢው የኤ ኤን ሲ ፓርቲ ሊቀመንበር በመሆን በድጋሚ ተመረጡ።ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የ2 ሺህ 476 መራጮች ድምፅ በማግኘት ነው በብርቱ የተፎካከሯቸውን ዝዌሊ ሚኪዜን አሸንፈው የኤ ኤን ሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ።ይሁንና ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ላይ ከቀረቡ የሙስና ክሶች ጋር በተያያዘ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ምርመራ ሊያካሂዱባቸው እንደሚችሉ ቢቢሲ ዘግቧል ።

🇺🇬#ኡጋንዳ ኡጋንዳ ከኢቦላ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በአገሪቱ ተጥለው የነበሩ የእንቅስቃሴ ክልከላዎችን አነሳች ።በኡጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝ የተሰራጨባቸው በነበሩ የሙበንዴ እና የካሳንድራ ግዛቶች በሽታው በቁጥጥር ስር በመዋሉ በግዛቶቹ ተላልፈው የነበሩ ገደቦች መነሳታቸውን ነው መንግስት ያስታወቀው።የኡጋንዳ የጤና ሚኒስቴር ባለፉት 42 ቀናት በኢቦላ የተያዘ አንድም ዜጋ አለመገኘቱን ይፋ እንዳደረገ አናዶሉ ዘግቧል ።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New