NewsSports

EBS SPORT- አርጀንቲና ከ36 አመታት በኋላ የአለም ዋንጫ አሸናፊ ሆናለች።

🇦🇷አርጀንቲና ከ36 አመታት በኋላ የአለም ዋንጫ አሸናፊ ሆናለች።

አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ እና አንሄል ዲማሪያ የመጀመሪያ አጋማሽ ግቦች 2ለ0 እየመራች ወደ መልበሻ ክፍል ብታመራም ኪሊያን ምባፔ በ98 ሰከንዶች ልዩነት በፍፁም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ያስቆጠራቸው ግቦች ጨዋታውን ወደ ጭማሪ ሰዓት አሸጋግረውታል።በጭማሪው ሰዓትም ሊዮኔል ሜሲ በጨዋታ ኪሊያን ምባፔ ደግሞ ሃትሪክ የሰራበትን ግብበፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠሩን ተከትሎ ጨዋታው 3ለ3 ተጠናቋል። በተሰጠው የመለያ ምትም አርጀንቲና 4ለ2 በመርታት የዋንጫው ባለቤት ሆናለች።ሊዮኔል ሜሲ በአለም ዋንጫ ታሪክ 25 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ የተጫወተ የመጀመሪያው ተጨዋች በመሆን ክብረወሰኑን በእጁ አስገብቷል ።ከዚህ በተጨማሪም በአለም ዋንጫ በ21 ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ አዲስ ታሪክ አጽፏል።አንሄል ዲማሪያ በአለም ዋንጫ እና በኮፓ አሜሪካ የፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው አርጀንቲናዊ ተጫዋች ሆኗል።ተጨዋቹ በኦሎምፒክ እና ፈይናሊዚማ የፍፃሜጨዋታላይም ኳስና መረብ ማገናኘቱ ይታወቃል ።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New