News

አዲስ ነገር – የአሜሪካ የ 55 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ እና ሌሎችም መረጃዎች

🇷🇺#ሩሲያ አሜሪካ ለዩክሬን ያቀደችው የሚሳኤል መከላከያ ስርዓትን እንዳትልክ ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች። ዋሽንግተን ለዩክሬን “ፓሮት” የተባለውን የሚሳኤል መከላከያ ስርአት የምትልክ ከሆነ ከሩስያ ጋር ወደ ቀጥታ ጦርነት ልትገባ እንደምትችል ነው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስጠነቀቀው።የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ወደ ዩክሬን የሚላኩ ማናቸውንም የጦር መሳርያዎች በቀጥታ ልንመታ እንችላለን ሲሉ መናገራቸውን አናዶሉ ዘግቧል ።

🇺🇸#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካ አፍሪካን በተጠናከረ ሁኔታ ለመደገፍ ዝግጁ ነች ሲሉ አስታወቁ ።በመካሄድ ላይ ባለው የአሜሪካ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የታደሙት ፕሬዚዳንት ባይደን በሚቀጥሉት 3 አመታት የሚተገበር የ 55 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርገዋል።ፕሬዚዳንት ባይደን “የአፍሪካ ስኬት የአሜሪካም ስኬት ነው ” ሲሉ በጉባኤው ለታደሙ የአፍሪካ መሪዎች ተናግረዋል።የባይደን አስተዳደር የአሜሪካ እና የአፍሪካ የንግድ ልውውጥ ያጠናክራል ተብሎ ከሚታሰበው የአፍሪካ የነጻ ንግድ ቀጠና ተቋም ጋር ስምምነት ሊደርሱ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።

#ኔቶ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት “ኔቶ ” አባል አገራት ለድርጅቱ የሚመድቡትን በጀት በ25 ከመቶ መጨመራቸው ተሰምቷል።በአውሮፓ የዩክሬን ጦርነት ባስከተለው የፀጥታ ስጋት ሳቢያ ነው የኔቶ አባል አገራት ከፈረንጆቹ 2023 ጀምሮ የኔቶ ድርጅት አመታዊ በጀት በ25 ከመቶ እንዲጨምር የተስማሙት።የኔቶ ዋና ፀሐፊ ጄንስ ስቶለንበርግ አባል አገራቱ የደረሱት የበጀት ጭማሪ በደስታ የምንቀበለው ነው ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል።

🇯🇵#ጃፓን ጃፓን አዲስ ልጅ ለሚወልዱ ጥንዶች የማበረታቻ ክፍያ ልትሰጥ መሆኑ ተሰምቷል።በአገሪቱ የህዝብ ቁጥር እድገት በእጅጉ በመቀነሱ ነው የቶኪዮ መንግስት ከአውሮፓውያኑ 2023 ጀምሮ በአገሪቱ ልጆች ለሚወልዱ ጥንዶች በነፍስ ወከፍ 592 ዶላር ለመስጠት ያቀደው።ይሁን እንጂ በጃፓን ካለው የኑሮ ውድነት አንፃር የአሁኑ የመንግስት ማበረታቻ ውጤታማ ላይሆን እንደሚችል መነገሩን የጀርመኑ ዶቸቨለ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New