News

አዲስ ነገር – ሱዳን በቀይ ባህር ጠረፍ አዲስ ወደብ እና ሌሎችም መረጃዎች

🇩🇪#ጀርመን የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ጠንካራ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታወቁ ።ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ይሄን ያሉት የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ሊሰጥ ያቀደውን ብድር የህብረቱ አባል አገር ሀንጋሪ ተቃውሞ ማሰማቷን ተከትሎ ነው ተብሏል።የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዎች እንዳይሳኩ መሰናክል የሚሆን አገር አይሳካለትም ሲሉ ቻንስለሩ መናገራቸውን ሬውተርስ ዘግቧል ።

🇨🇩#ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ የሞቱ ሰዎች ቁጥር በትንሹ 120 ደርሷል።በአገሪቱ መዲና ኪንሻሳ ባጋጠመው በዚሁ የጐርፍ አደጋ በትንሹ 120 ሰዎች መሞታቸው ሲነገር ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካቶች መጐዳታቸው ነው የተዘገበው ።የ12 ሚሊየን ሰዎች መኖሪያ በሆነችው ኪንሻሳ ከተማ በደረሰው የጐርፍ መጥለቅለቁ በርካታ የንብረት ውድመት ማጋጠሙን አልጀዚራ ዘግቧል።

🇸🇩#ሱዳን ሱዳን በቀይ ባህር ጠረፍ አዲስ ወደብ ለማስገንባት ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኩባንያዎች ጋር ከስምምነት ደረሰች ።የካርቱም መንግስት በቀይ ባህር ጠረፍ አዲስ ወደብ ለማስገንባት ከአረብ ኢምሬቶቹ የአቡዳቢ ፓርትስ እና የኢንቪክተስ ኩባንያዎች ጋር የ6 ቢሊየን ዶላር ስምምነት መፈራረሙ ነው የተነገረው።የሱዳን የገንዘብ ሚኒስቴር አዲሱ ወደብ ግዙፍ የአየር ማረፊያን ጨምሮ የነፃ የንግድ ቀጠና ያካተተ እንደሆነ ማስታወቁን ኤፒ ዘግቧል።

🇬🇭#ጋናየጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ የአፍሪካ አገራት ከልመና እንዲቆጠቡ ጥሪ አቀረቡ።በመካሄድ ላይ ባለው የአሜሪካ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ የታደሙት ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ የአፍሪካ አገራት ከምዕራባዊያን እርዳታ ከመጠየቅ በመቆጠብ አፍሪካ በራሱ የቆመ አህጉር እንዲሆን ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ የገንዘብ አቅም ያላቸው የአፍሪካ ዜጎች ገንዘባቸውን ወደ ሌላ አገራት ከመላክ በአፍሪካ መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ የአፍሪካ እድገትን ሊያረጋግጡ ይገባል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New