Sports

EBS SPORT – ፈረንሳይ ሞሮኮን 2ለ0 በመርታት የፍፃሜ ተፋላሚ ሆናለች።

🇫🇷ፈረንሳይ ሞሮኮን 2ለ0 በመርታት የፍፃሜ ተፋላሚ ሆናለች። ሰማያዊዎቹን ባለድል ያደረጉትን ግቦች ቲዮ ሄርናንዴዝ እና ተቀይሮ የገባው ኮሎ ምዋኒ በስማቸው አስመዝግበዋል ። ምዋኒ ተቀይሮ በገባ 44ተኛው ሰከንድ ያስቆጠራት ግብም በአለም ዋንጫ ታሪክ ሶስተኛዋ ፈጣን ግብ ሆናለች።ፈረንሳይ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የፍፃሜ ተፋላሚ የሆነች ስድስተኛዋ ሃገር ለመሆን ችላለች።ለመጨረሻ ጊዜ በተከታታይ የፍፃሜ ተፋላሚ የነበረችው ብራዚል በ1994 እና 1998 እንደነበር ይታወሳል። አንትዋን ግሬዝማን ለፈረንሳይ በ18 ተከታታይ የአለም ዋንጫዎች ላይ በመሰለፍ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።ዲዲየር ዴሾ ለሁለት ተከታታይ የፍፃሜ ጨዋታ የደረሰ አራተኛው አሰልጣኝ ለመሆን በቅቷል። በጨዋታው የሞሮኮው አጥቂ ዩሱፍ ኢኒስሪ ተቀይሮ እስኪወጣ ድረስ ሶስት ኳሶችን ብቻ የነካ ሲሆን ከ1966 በኋላ ቢያንስ 45 ደቂቃ ተጫውቶ ጥቂት ኳስ የነካ ተጫዋች ሆኗል።

⚽ 22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ የደረጃ ጨዋታ #ቅዳሜ ታህሳስ 8, 2015 አንድ መርሃ ግብር ይደረጋል። 👉 ክሮሺያ🇭🇷🇲🇦ሞሮኮ – 12:00 ምሽት

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New