EBS SPORT – የኢትዮጵያ እና የግብጽ የዛሬ ምሽት ጨዋታ እና ሌሎች መረጃዎች
👉🏾 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወሳኙን ጨዋታ ዛሬ ምሽት ከግብጽ ብሄራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል
በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በማላዊ 2 ለ 1 የተረታው ዋልያው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን ከፈሮኖቹ ጋር ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት የሚያደርግ ይሆናል በአሰልጣኝ ውብቱ አባተ የሚመራው ቡድኑ በቢሾፕ ማኬንዚ ትምህርት ቤት ሜዳ ዝግጅቱን አጠናክሮ ሲሰራ የቆየ ሲሆን አሰልጣኙም ለጨዋታው ትኩረት ሰተው እንደሚጫወቱ ጠቁመዋል
👉🏾 በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ማሳካት ችላለች
በሞሪሺየስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ አለም ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በትላንትናው አለት በ 10 ሺ ሜትር ወንዶች በአትሌት ሞገስ ጥኡማይ አማካኝነት የወርቅ ሜዳሊያን ማሳካት ስትችል አትሌት ጭምዴሳ ደበላ በውድድሩ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ማስገኘት ችሏል
👉🏾 በዜግነቱ ፊንላንዳዊ የሆነው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዊሊያም አላታሎ ከኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት አሶሴሽን ጋር በጋራ ለመስራት መስማማቱ ተጠቁሟል
በአለም አቀፍ ደረጃ የፈጣን የመኪና እሽቅድድሞሽ ተወዳዳሪው የሆነው ዊሊያም በውድድር ዘርፉ የተለያዩ አለም አቀፍ ሽልማቶችን ማግኘት የቻለ ሲሆን ያካበተውን አለም አቀፍ ልምድም ለሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች ለማካፈልና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል
👉🏾 የኤቨርተኑ ባለቤት ፈርሃድ ሞሽሪ ክለባቸው አስቸጋሪ የውድድር አመትን ማሳለፉን ተከትሎ ደጋፊዎችን ይቅርታ ጠይቀዋል
ክለቡን በባለቤትነችዠት ከተረከቡበት 2016 አንስቶ ለተጨዋቾች ዝውውር ከ 500 ሺ ፓወንድ በላይ ወጪ ቢያደርጉም ከረሜላዎቹ ግን በሊጉ ያን ያህል መድመቅ አልቻሉም በዚህም የክለቡ ባለቤት ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ በመጠየቅ ከዚህ የቸሻለ ነገር መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል
👉🏾 የሪያል ማድሪዱ የመሃል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች በሪያል ማድሪድ ለተጨማሪ 1 አመት የሚያቆየውን አዲስ ውል ፈርሟል
በ2012 የውድድር አመት ከቶትንሃም ሎስብላንኮሶቹን መቀላቀል የቻለው የባላንዶር አሸናፊው እስካሁን ድረስ በነጩ ማሊያ 436 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ሲችል የላሊጋና የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ ሌሎች ክብሮችን ተጎናጽፏል
👉🏾 ሞሃመድ ሳላ እና ቡካዮ ሳካ በየክለባቸው የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብለው ተመርጠዋል
ከሊቨርፑል ጋር ምርጥ የውድድር አመትን ማሳለፍ የቻለው ሳላ በውድድር አመቱ በሁሉም ውድድሮች 31 ጎሎችን በማስቆጠርና 15 ጎል የሆኑ ኳሶችን በማቀበል የሊቨርፑል የስታንዳርድ ቻርተርድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ሲችል በአርሰናል ድንቅ የውድድር አመትን ማሳለፍ የቻለው ሳካ በበኩሉ በተከታታይ አመት የመድፈኞቹ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ ተመርጧል
👉🏾 ማንችስተር ዪናይትድ ለፍራንክ ዲዮንግ ዝውውር 80 ሚሊዮን ዩሮ ማቅረቡ ተጠቁሟል
አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ከተጨዋቹ ጋር በአያክሰ ጥሩ የውድድር አመት ማሳለፋቸውን ተከትሎ ተጨዋቹን ወደ ኦልትራፈርድ ለማምጣት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል ባርሴሎናም ዲዮንግን በ 80 ሚሊዮን ዩሮ ለመሸጥ ፍቃደኛ መሆኑ ተገልጿል
👉🏾 የሌስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ሪቻርልሰን መዘዋወር የሚፈልግባቸውን 3 ክለቦች ይፋ አድርጓል
ተጨዋቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከቀበሮዎቹ ጋር መለያየት እንደሚፈልግ ማሳወቁ የሚታወስ ሲሆን ፒ ኤስ ጂ ሪያል ማድሪድ እና ቼልሲ ምርጫዎቹ መሆናቸውን በመግለፅ ወደ አርሰናል የማምራት ፍላጎት እንደሌለው ጠቁሟል
👉🏾 የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል ባየርሙኒክ ሳዲዮ ማኔን ለማስፈረም ያቀረበውን የዝውውር ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ ውድቅ አድርጓል
የተጨዋቹ ፈላጊ ከሆኑ ክለቦች መካከል በቀዳሚነት የተቀመጠው ባየርሙኒክ ለሁለተኛ ጊዜ ባቀረበው የተሻሻለ የዝውውር ጥያቄም ለ ዝውውር 23.5 ሚሊዮን ፓወንድ ለመክፈል የተስማማ ሲሆን ሊቨርፑል በቀጣዮቹ 3 ተከታታይ አመታት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ካነሳ እንዲሁም ተጨዋቹ 3 ጊዜያት ያህል ባላንዶርን ካሸነፈ ተጨማሪ 6ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓወንድ ለቀዮቹ ለመክፈል ጥያቄ ቢያቅርብም የአንፊልዱ ክለብ ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New