Sports

EBS SPORT- አርጀንቲና ክሮሺያን 3ለ0 በመርታት ለፍፃሜው ጨዋታ አልፋለች።

🇦🇷አርጀንቲና ክሮሺያን 3ለ0 በመርታት ለፍፃሜው ጨዋታ አልፋለች። ሁለቱን ግቦች ዩሊያን አልቫሬዝ ሲያስቆጥር ቀሪዋን አንድ ግብ ሊዮኔል ሜሲ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል።ሊዮኔል ሜሲ በአለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን ግቦች አስራ አንድ በማድረስ የአርጀንቲና የምንግዜም ከፍተኛ አስቆጣሪ ሲሆን በአለም ዋንጫ 8 ግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበልም የማራዶናን ክብረወሰን ተጋርቷል። ሜሲ በአራት የተለያዩ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ግብ አስቆጥሮ ግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ በማቀበል የመጀመሪያው ተጨዋች ለመሆንም ችሏል።ከዚህ ባለፈም በአምስት ግቦች የኮኮብ ግብ አግቢነቱን ከምባፔ ጋር መምራት ጀምሯል። አርጀንቲና በአለም ዋንጫ ለግማሽ ፍፃሜ በደረሰችባቸው አምስት አጋጣሚዎች በሙሉ ለፍፃሜ ደርሳለች።

⚽ 22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ረቡዕ ታህሳስ 5, 2015 አንድ መርሃ ግብር ይደረጋል። 👉 ፈረንሳይ🇫🇷🇲🇦ሞሮኮ – 4:00 ምሽት

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New