EthiopiaNews

ለአሜሪካ ጉዞ የማስያዣ ገንዘብ

🔸ከነገ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ተጓዦች የቪዛ ዋስትና ገንዘብ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

🔸ኢትዮጵያ የቪዛ ዋስትና ገንዘብ ከሚጠየቁ ሀገራት ወስጥ መካተቷን ያስታወሰው ኤምባሲው ለንግድ ወይም ለጉብኘት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ብቁ ሆነው የተገኙ የቪዛ አመልካቾች ቪዛው ከመሰጠቱ በፊት እስከ 15ሺ ዶላር በዋስትና እንዲያስይዙ እንደሚገደዱም ጠቅሷል፡፡

🔸ሆኖም ተጓዦች የቪዛውን ህግና ደንቦች በሙሉ አክብረው ከተገኙና የተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ ሳያበቃ ከአሜሪካ ከተመለሱ ያስያዙት የገንዘብ ዋስትና ተመላሽ እንደሚሆን ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews