ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባው 3 ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡
የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስና የኢትዮጵያ ካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጆችን አፀደቀ።
የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በታክስ ከፋዩና በታክስ ሰብሳቢው የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት፣ ተጠያቂነትና ፍትሐዊነትን ለማስፈን ብሎም ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም የኢትዮጵያ ካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅ እያደገ የመጣውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ወደ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሻገር፣ የአረንጓዴ ኢንቨስትመንትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ የሚረዳ ነው ብለዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
