በሳዑዲ አረቢያ ምሕረት ከተደረገላቸው ኢትዮጵያውያን መካከል 320ዎቹ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ ምሕረት ከተደረገላቸው ኢትዮጵያውያን መካከል 320ዎቹ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን አስታወቀ።
ከሳዑዲ የተመለሱት ኢትዮጵያውያን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1655 ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ ምሕረት እንደተደረገላቸው ይታወሳል።
ይህ ውጤት መንግሥት በውጭ ግንኙነቱ ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት የተገኘ ነው ሚነስቴሩ ገልጿል። መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
