EthiopiaNews

በቁጥጥር ስር የዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች

የገቢዎች ሚኒስቴር ከ890 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ።

የጉምሩክ ኮሚሽን ከሚያዚያ 8 እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 872.2 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 18 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 890.2 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ጥፍጥፍ ወርቅ፣ የተለያዩ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት ፣ አዋሽ እና ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 450 ሚሊዮን ፣ 126 ሚሊዮን እና 108 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 43 ተጠርጣሪዎች እና ሰባት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

መረጃው ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv