በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
አንድ የአሜሪካ ፊደራል ፍርድቤት የፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ለሚኖሩ ከ5ሺ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን የሕግ ከለላ ለማቋረጥ እና ከአገር ለማባረር የደረሰውን ውሳኔ አገደ፡፡
አስተዳደሩ የወሰደው እርምጃ በሀገሪቱ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሆኑ ከሌሎች ግጭት ወይንም አለመረጋጋት ካለባቸው ሀገራት የመጡ ዜጎች በጊዜያዊነት ጥበቃ የሚደረግበትን ሁኔታ ወይም ቲፒኤስ ተብሎ የሚጠራው የህግ ከለላ እንዲቋረጥ እንደሚያደርግ የተነገረ ሲሆን ስደተኞቹ በህጋዊ መንገድ እየሰሩ እንዳይኖሩና እንዳይሰሩ ብሎም ከሀገሪቱ እንዲባረሩ የሚያስገድድ እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡
ሆኖም የፌደራሉ ዳኛ ውሳኔ አስተዳደሩ ተገቢውን ህጋዊ አካሄድ ያልተከተለ እና ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ውሳኔውን ማገዱ ነው የተሰማው፡፡ ውሳኔው ጊዜያዊ እፎይታን ቢሰጥም የስደተኞቹ የወደፊት እጣ ፈንታው ገና በሂደት ላይ ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡
የባይደን አስተዳደር ከ2022 ጀምሮ የአፍሪካ ሀገራት ዜጎችን ከጦርነት እና ከሰብአዊ ቀውስ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ በመጥቀስ ይህን ህግ ያወጣ የመጀመሪያው አስተዳደር መሆኑ ይታወሳል፡፡ የህጉ ተገባራዊነት በፈረንጆቹ 2024 ተራዝሞም ነበር፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
