በአዲስ አበባ አዲሱ የተሽከርካሪ ሠሌዳ መሰጠት መጀመሩን የከተማዋ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።
አዲሱ ሠሌዳ ሀገራዊ የሆኑ ይዘቶችን ያካተተ መሆኑን እና ኮፒ ወይም ፎርጂድ የማይሠራበት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አገልግሎቱን ለማዘመንና ቁጥጥሩን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝም ጠቁሟል።
ለዚህም አዲሱን የተሽከርካሪ ሠሌዳ አጠቃላይ ይዘት አተገባበር ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ሥራዎችን ለማዘመን እንዲሁም ኢትዮጵያን የሚገልጹ መለያዎችን የያዘና ዓለም አቀፍ መስፈርቱን የተከተለ ነው ተብሏል።
እንዲሁም ሠሌዳው የተለያዩ መረጃዎችን የሚይዝ በመሆኑ ለሕግ ማስከበር ሥራ የሚመች፣ ቶሎ የማይበላሽና ወጪ ቆጣቢ ነው የተባለ ሲሆን ተግባራዊ ለማድረግም አዲስ ለሚገዙ መኪኖች አገልግሎቶች የሚጀመር መሆኑን እና ከዚህ በፊት ሠሌዳ ለሌላቸው አገልግሎቱ በቅርብ እንደሚጀመርም ተጠቁሟል።
ሠሌዳው ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ መሰጠት መጀመሩንና ተገልጋዮች በተመዘገቡበት ቅደም ተከተል እንደሚወስዱ እንዲሁም በክልል ከተሞች ደግሞ በቅርቡ የሚጀመር ይሆናል ተብሏል። መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
