በኢትዮጵያ እስከ 50 ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ አይደሉም ተባለ።
የውኃና እነርጂ ሚኒስቴር እስከ 50 ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ አለመሆናቸውን አሳውቋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ያሳወቀው በቀጣዮቹ 4 ዓመታት የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ ያልሆኑ ዜጎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን መቶ በመቶ ለማሳካት አዲስ የውሃና ሳኒቴሽን አስተዳደር ሞዴል ማዘጋጀቱን በገለጸበት ወቅት ነው።
የውኃና እነርጂ ሚኒስቴር አክሎም ከልማት አጋሮችና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከ230 ሺህ በላይ የውሃ ተቋማትን በመገንባት ከ82 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረጉን አሳውቋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
