በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ
የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ማዕቀፍ ግልጽ፣ ምላሽ ሰጪና በሰብአዊ መብቶች መርሖች ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ተጠይቋል፡፡
ይህ የተጠየቀው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጎጂዎች እውነትን የማወቅ መብትና ክብር ዓለም አቀፍ ቀንን አስመልክቶ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ሲሆን እውነትን የማወቅ መብት ተጠያቂነት ለማረጋገጥ፣ እርቅን ለማውረድና ወደፊት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ዳግም እንዳይከሰቱ ለመከላከል አስተዋጾ እንዳለው ተጠቁሟል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ማዕቀፍ እውነትን የማፈላለግ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት ሂደቱ ግልጽነት ያለው፣ ምላሽ ሰጪና በሰብአዊ መብቶች መርሖች ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
