EthiopiaNews

በኢትዮጵያ የቱሪስቶች የቆይታ ጊዜ ከ7 ቀናት ወደ 16 ቀናት ማደጉን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የቱሪስቶች አማካይ የቆይታ ጊዜ ከ7 ቀናት ወደ 16 ቀናት ከፍ ማለቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ በርካታ ተፈጥሯዊ እንዲሁም የባህልና ሰው ሰራሽ መስህቦች ቢኖሯትም ከዘርፉ የሚገባትን ያህል ተጠቃሚ ሳትሆን ቆይታለች ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማደስ፣ እንዲሁም አዳዲስ መዳረሻዎችንና መሠረተ ልማቶችን የመገንባት ሥራ በመከናወኑ የቱሪስቶች አማካይ የቆይታ ጊዜ መሻሻሉን ጠቁመዋል።

ቀደም ሲል ከ5 እስከ 7 ቀናት ብቻ የነበረው የአንድ ቱሪስት አማካይ የቆይታ ጊዜ በአሁኑ ወቅት ወደ 16 ቀናት ከፍ ማለቱን ሚኒስትር ዴኤታ ጨምረው ተናግረዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews