EthiopiaNews

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዝ አስገዳጅ ሊሆን ነው ተባለ።

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዝ አስገዳጅ እንደሚሆን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት በኮንስትራክሽን ዘርፉ ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ያሉ ባለሙያዎች በአግባቡ ሰልጥነው፣ ህጋዊ የሰርቲፊኬሽን ስርዓት ውስጥ አልፈው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን አሰራር ደረጃ በደረጃ በማሳደግ ሰርተፊኬት የሌላቸው ባለሙያዎች በየትኛውም ደረጃ በሚገኙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ሙሉ በሙሉ አስገዳጅ እንደሚሆንም ነው የገለጹት፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews