ታዋቂው ቲክቶከር ዲላን ፔጅ በአዲስ አበባ
በፈጣን ዜና አቀራረቡ የሚታወቀው እና ከ19 ሚሊዮን በላይ የቲክቶክ ተከታዮችን ማፍራት የቻለው ዝነኛው የይዘት ፈጣሪ ዲላን ፔጅ ከኢትዮጵያዊው ቲክቶከር አዶናይ ጋር አዲስ አበባ መግባቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
ታዋቂው ቲክ ቶከሩ ዲላን ወደ ኢትዮጵያ በአካል ሲመጣ የመጀመሪያው ሲሆን ኢትዮጵያ በመምጣቱ ደስተኛ መሆኑን እና የአዲስ አበባ ውበት እንዳስደመመው ገልጿል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር ዲላን ስለ ኢትዮጵያ በርካታ አዎንታዊ ይዘቶችን ለዓለም በማቅረብ እንደሚታወቅ ገልጾ በተለይም ስለ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ምርቃት በሰራው ዘገባ ምርቃቱ ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጾ እንደነበር አስታውሷል።
ዘገባው “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የሚቀይረው የአፍሪካ የብርሃን ተስፋ” በማለት ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ተብሏል።
የቲክቶከሩ ዲላን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ በማስተዋወቅ ፣ለዲጂታል ዲፕሎማሲው ስኬት እና የኢትዮጵያን እውነታ ለዓለም ማኅበረሰብ ለማሳየት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በሚኒስቴሩ መግለጫ ተጠቁሟል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/