InternationalNews

አይኤም ኤፍ ለኢትዮጵያ የሚለቀውን የ468 ሚሊዮን ዶላር ብድርን ለማፅደቅ የስራ አስፈፃሚ ቦርዱ የፊታችን ረቡዕ ሊሰበሰብ ነው።

የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚለቀውን የ468 ሚሊዮን ዶላር ብድርን ለማፅደቅ የስራ አስፈፃሚ ቦርዱ የፊታችን ረቡዕ እንደሚሰበሰብ ተነገረ።

የአይ ኤም ኤፍ ቃል አቀባይ ጁሊ ኮዛክ ከአንድ ወር በፊት ኢትዮጵያ እና አይ ኤምኤፍ በአምስተኛው ዙር የተራዘመ ብድር አቅርቦት ላይ በባለሙያዎች ደረጃ ከስምምነት መድረሳቸውን አስታውሰው የስራ አስፈፃሚ ቦርዱ በረቡዕ ስብሰባው ስምምነቱን ካፀደቀ ሀገሪቱ 468 ሚሊየን ዶላር እንደሚለቀቅላት ነው የተናገሩት።

ቃል አቀባይዋ ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ 468 ሚሊየን ዶላር ካገኘች አጠቃላይ ከገንዘብ ድርጅቱ ያገኘችው ገንዘብ 2.6 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል ብለዋል።

ጁሊ ኮዛክ ኢትዮጵያ ከገንዘብ ድርጅቱ ከምታገኘው 468 ሚሊየን ዶላር ውስጥ 200 ሚሊየን ዶላሩ የኢራን ጦርነት ያደረሰውን የአቅርቦት ጫና እንድትቋቋም በሚል የሚለቀቅላት ነው ብለዋል። መረጃው ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews