EthiopiaNews

አዲሱ የህግ ትርጉም

ከእረፍትና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ ለአምስት ተከታታይ ቀናትና ከዚያ በላይ ከስራ የቀረ ሰራተኛን ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውልን ማቋረጥ የሚያስችል አዲስ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡

ይህን ህግ ትርጉም የሰጠው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በተከታታይ ቀናት ከሥራ ለሚቀሩ ሠራተኞች ከሥራ ሊባረሩ በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ ከዚህ ቀደም የተሠጠውን የሕግ ትርጉም በመሻር ነው አዲስ ትርጉም የሰጠው።

ካሁን በፊት በተሠጠ የሕግ ትርጉም አንድ ሠራተኛ በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ቢቀር ከሥራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሠሪው ማስጠንቀቂያ ሳይሠጥ የሠራተኛውን የሥራ ውል ማቋረጥ እንደማይችል የሚገልጽ ነበር።

ኾኖም ሠበር ሰሚ ችሎቱ ይህን የሕግ ትርጉም መሻሩን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ባሠራጨው ዝርዝር የሕግ ትርጉም መግለጫ አስታውቋል።

ችሎቱ ነባሩን የሕግ ትርጉም በማሻሻል ሠራተኛው በዚሁ አዋጅ ከተመለከቱ እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ውጭ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ከቀረ፣ አሠሪው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳይገደድ የሥራ ውልን ያለ ማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ይቻላል በሚል ነው የተረጎመው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv