አዲስ ነገር – የህግ ማስከበር ዘመቻ
በአማራ ክልል የኢንቨስትመንትና ሌሎች መንግስታዊ ስራዎች እንዳይከናወኑ እንቅፋት የሚፈጥሩ ሁኔታዎች እየታዩ መምጣታቸው ተነግሯል፡፡
ይህ የተነገረው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በክልሉ ወቅታዊ የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ዙሪያ ትላንት ከሰዓት በሰጡት መግለጫ ሲሆን የሕገወጥ ንግድ መበራከት፣ ምርቶችን በመደበቅ ሰው ሰራሽ እጥረት መፍጠር፣ ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ የጥይት ተኩስና መሰል ያልተገቡ እንቅስቃሴዎች በክልሉ እየተስተዋሉ ነው ብለዋል።
ከዚህ አልፎም በየቦታው የታጠቀም ሆነ ያልታጠቀ ኃይል በጉልበት የመዝረፍና ሰው ማገት እንዲሁም ሕዝብን እርስ በእርስ በሃይማኖት፣ በብሔርና መሰል ጉዳዮች በመከፋፈል ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል ሲሉ ተደምጠዋል።
መሰሎቹ ሕገወጥ ተግባራት ሕዝቡን የጸጥታ ስጋት ውስጥ ከተውታል ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ የክልሉ መንግስት ጠንካራ የሕግ ማስክበር ስራ ጀምሯል፤ ሕገ ወጦችም በቁጥጥር ስር እየዋሉ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ዘመቻው የአማራ ክልልን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ የሕብረተሰቡን የጸጥታ ስጋትና ተንቀሳቅሶ የመስራት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የሚከናወን እንደሆነ የገለጹት ርዕሰ መስተዳደሩ ከሰሞኑን በክልሉ የተጀመረው የመሳሪያ ምዝገባ ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡
መረጃውን ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንና ከኢዜአ ተመልክተነዋል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New