News

አዲስ ነገር – የሰሜን ኢትዮጵያ ነገር

መንግስት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህውሃት ቡድን እየቀጠለ ያለው ትንኮሳ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመትን ከማስከተሉ በፊት አለምአቀፉ ማህበረሰብ ሊያወግዘው እንዲሁም ከፀብ ጫሪ ድርጊቱ እንዲታቀብ ግፊት እንዲያደርግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።

ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ይህንን ያሉት ከአውሮፓ ህብረት የሰብአዊ መብቶች ልዩ ተወካይ ኤሞን ጊልሞር ጋር በሰብአዊ መብት ጉዳዮችና በሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነት እንዲሁም መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥ እየወሰዳቸው በሚገኙ እርምጃዎች ዙሪያ ውይይት ባደረጉበት ጊዜ ነው፡፡

የአውሮፓ ህብረት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ልዩ ተወካይ ኤሞር ጊሊሞር በበኩላቸው ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎች በሁለቱም ወገኖች እየተሰሩ መሆኑን አንስተው መንግስት ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ በጦር ቀጠና ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ የተኩስ አቁም ካደረገ በኋላ ነባራዊ ሁኔታዎች መሻሻላቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በነበረው ጦርነት የሰብአዊ መብት ጥሰትና ወንጀሎችን የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች ተጠያቂ የማድረጉ ሂደት እንዲፋጠን መጠየቃቸውንና ሰብዓዊ ድጋፎችም በበቂ ሁኔታ ለማድረስ ሁሉም አካል ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል። መረጃዉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ነው ያገኘነው፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New