Sports

EBS SPORT – አጫጭር የኢቢኤስ ስፖርት ዘገባዎች / ግንቦት 11/2014

✍🏼 የኢትዮጵያ ከ 17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በነገው እለት ወሳኙን ጨዋታ ያደርጋል
በህንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ከ 17 አመት በታች ውድድር ለማለፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ የሚገኙት እንስቶቹ የመጨረሻ የማጣርያ የደርሶ መልስ ጨዋታቸውን ከናይጄሪያ ጋር የሚያደርጉ ሲሆን የመጀመሪያው የማጣርያ ጨዋታም በነገው እለት በአበበ ቢቂላ ስታድየም የሚደረግ ይሆናል

✍🏼 አዳማ ከተማ ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር መለያየቱ ተነግሯል
ቅዱስ ጊዮርጊስን በምክትል አሰልጣኝነት እንዲሁም ባህርዳር ከተማን በዋና አሰልጣኝነት መምራት የቻለው ፋሲል በውድድር አመቱ መጀመሪያ አዳማ ከተማን ለማሰልጠን መረከቡ የሚታወስ ሲሆን ከውጤት ጋር በተያያዘ ከቡድኑ ጋር እንደማይቀጥል ከክለቡ አመራሮች ጋር ባደረገው ውይይት ተረጋግጧል


✍🏼 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ የውድድር ዓመት የሚጀመርበት ቀን ይፋ ተደርጓል
የዘንድሮው የውድድር አመት በመጪው ሰኔ 24 እንደሚጠናቀቅ አስቀድሞ የተገለፀ ሲሆን ፕሪምየር ሊጉን እየመራ የሚገኘው አክስዮን ማህበሩም የ2015 የውድድር አመት መስከረም 20 እንደሚጀመር አስታውቋል የክረምቱ የዝውውር መስኮትም ሀምሌ 1 በይፋ እንደሚከፈት አያይዞ ገልጿል


✍🏼 በሴካፋ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በትላንትናው እለት የመጀመሪያ ልምምዱን ማከናወኑን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል
ውድድሩ በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከ ግንቦት 24 እስከ ሰኔ 3 የሚደረግ ሲሆን አሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብሬልም ለ 23 ተጨዋቾች ጥሪ በማቅረብ በ35 ሜዳ ልምምድ መጀመሩ ተጠቁሟል


✍🏼 ኢንትራከት ፍራንክፈርት ሬንጀርስን በማሸነፍ የኢሮፓ ሊግ ዋንጫን ማሳካት ችሏል
ሁለቱ ክለቦች በመደበኛውና በጭማሪው 30 ደቂቃ 1-1 መለያየታቸውን ተከትሎ ወደ መለያ ምት ያመሩ ሲሆን የጀርመኑ ክለብም 5-4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋንጫውን የግሉ አድርጓል
ድሉን ተከትሎም ክለቡ ከ1996/97 የውድድር አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ዋንጫ መሳም የቻለ የመጀመሪያው የጀርመን ክለብ እንዲሆን አስችሎታል

✍🏼 ጋቦናዊው አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦበምያንግ ከሀገሩ ብሄራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል
ጋቦንን በአምበልነት መምራት የቻለው የባርሴሎናው ተጨዋች ለ13 አመታት ያህል ሀገሩን ወክሎ መጫወት የቻለ ሲሆን በ 72 ጨዋታዎችም 30 ጎሎችን ከመረብ በማሳረፍ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆኑ ይታወቃል

✍🏼 ማንችስተር ሲቲ ኬቨን ፕሊፕስን የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተጠቁሟል
የውሃ ሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ፕሊፕስን የፈርናንዲኒሆ ተተኪ ለማድረግ እያጤኑ እንደሚገኙ ተነግሯል ማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቹን ለማስፈረም እንደሚፈልግ ሲነገር ቢቆይም ኬቨን

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New