News

አዲስ ነገር – የኦዲት ግኝት ማስተካከያ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ የኦዲት ግኝት ማስተካከያ እያጣራ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅርንጫፍ በመገኘት፣ የዋና ኦዲተር የ2012 እና 2013 በጀት ዓመት የክዋኔ ኦዲት ግኝት ላይ ማስተካከያ መደረጉን እያጣራ ያለው ኮሚቴው ከምልከታው አስቀድሞ የክዋኔ ኦዲት ግኝትን በተመለከተ፤ ከጉሙሩክ ኮሚሽን አመራሮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል ተብሏል፡፡
በዋና ኦዲተር የቀረበው የክዋኔ ኦዲት ግኝት የማስተካካያ ርምጃ ስለመወሰዱ ከሚያጣራው ኮሚቴ ጋር ከፌዴራል ዋና ኦዲተር፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከግዥ እና ንብረት ባለስልጣን፣ ከመንግስት ግዥ አገልግሎት እና ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የተውጣጡ ባለሙያዎች በተባባሪነት በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማህበራዊ የትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New