News

አዲስ ነገር – የገንዘብ ሚኒስቴርና ኤፍኤስዲ አፍሪካ

የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኢንቭስትመት ሆልዲንግ እና በምጻረ ቃሉ ኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ ከተሰኘ ተቋም ጋር የኢትዮጵያ ሴኪዩሪቲ ኤክስቼንጅን ለማቋቋም የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ተነገረ፡፡
ለኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት ለሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረክ ይሆናል የተባለለት ይህ ስምምነት በአፍሪካ 30ኛው የልውውጥ መንገድ ሲሆን በመንግስት ብቻ የተያዙ መስኮች የግሉ ዘርፍ እንዲሳተፍባቸው አቅም የሚሰጥ መሆኑን ኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ በድረገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ መንግስት ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን እያደረገ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ፕላትፎርም የተጀመረውን ስራ ለማቀላጠፍ ብሎም በግሉ ዘርፍ የሚሳተፉ ባለሃብቶችን ለመሳብ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New