News

አዲስ ነገር – የተሻሻለው የግድቡ መንገድ

ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚጓጓዙየግንባታ ግብአቶች ወደ ስፍራው ለመድረስ ይደርስባቸው የነበረውን መስተጓጎል ይቀንሳል የተባለ የመንገድ ስራ መጠናቀቁ ተነግሯል፡፡

ከግልገል በለስ እስከ አባይ ግድብ የሚያደርሰው ይህ መንገድ ከመሰራቱ በፊት ግአቶችን ወደ ግድቡ ለማጓጓዝ አንድ ሳምንት ድረስ ይፈጅ ነበር የተባለ ሲሆን አሁን በተሰራው መንገድ የተነሳ ግን በአንድ ቀን ጉዞ ግብአቶቹን ወደ ግድቡ ማድረስ እንዲቻል ሆኗል ነው የተባለው፡፡

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የተሰራው ይህ መንገድ 210 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለውን 3ኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ ወደ ከፍተኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ ያሳደገ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ግንባታውም በተቀመጠለት የግዜ ሠሌዳ መጠናቀቁ ነው የተሰማው።

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የግልገል በለስ-አባይ ግድብ የመንገድ ፕሮጀክትን ስራ ሲረከብ የተሠጠው የመንገድ ፕሮጀክት ስራ ብቻ ሳይሆን ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነትና አደራም እንደነበር የተጠቆመ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም የመምሪያው የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም ባለስልጣናት መርቀውታል፡፡
መረጃው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ነው ፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New