አዲስ ነገር – የኢትዮጵያና ኖርዌይ ስምምነት
ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥን የሚመለከቱ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ተነገረ፡፡
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ የኖርዌይ የአየር ንብረትና አካባቢ ሚኒስቴር ልዩ ልዑክን በቢሮዋቸው ተቀብለው ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ አጠቃላይ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸው ተመልክቷል፡፡
እንዲሁም የኖርዌይ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አስመልክቶ ሊያዘጋጅ ስላለው የሁለተኛ ምዕራፍ የስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት ግብዓት የሚሆነውን የመንግስትን አቅጣጫ በመዳሰስ የመከሩ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም አደረጃጀቱን ማሻሻሉንና ሁሉም ዘርፎች የአየር ንብረት ለውጥና አካባቢ ጉዳይን አካተው እንዲያቅዱና እንዲፈጽሙ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡
በእቅድና ፖሊሲ ደረጃ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ኢኮኖሚ መገንባት ላይ ኢትዮጵያ አሁንም አጠናክራ መቀጠሏ የተጠቀሰ ሲሆን በአየር ንብረት ዘርፍ ኢትዮጵያ የኖርዌይ መንግስት ከሚሰጠው ድጋፍ በአፍሪካ ውስጥ ትልቋ ተጠቃሚ እንደነበረች በማንሳት በቀጣይም ኢትዮጵያ በቀጠናው ካላት ከፍተኛ ሚና አንፃር በባዮ ዳይቨርሲቲ፣ በደን ማልማትና በዘላቂ ልማት ዙሪያ በሰፊው ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥል መገለጹን ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የማህበራዊ የትስስር ገጽ ተመልክተናል።
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New