News

አዲስ ነገር – ምርጥ የህዝብ አገልግሎት

በገንዘብ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን የተመራውና የቴሌኮም ዘርፍን ለውድድር ክፍት በማድረግ ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተሰጠው አዲስ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፍቃድ ሂደት፥ በምርጥ የሕዝብ አገልግሎት ፕሮጀክት ምድብ አሸናፊ ሆኖ መመረጡ ተነገረ፡፡

የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጡ ሂደት በልማት አጋር ሽልማት ወይም ፓርትነርሺፕ አዋርድስ ድርጅት እ.ኤ.አ የ2022 አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው በኢነርጂ፣ በውሀና በቴሌኮም ዘርፍ ምድብ ሲሆን ሽልማቱም ለገንዘብ ሚኒስቴር የተበረከተው ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም በእንግሊዝ ሀገር ለንደን ከተማ በተደረገ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፍቃድ ሂደቱ በአንደኛነት የተመረጠው ከአምስት የተለያዩ በአገልግሎት ዘርፍ በእጩነት ቀርበው ከነበሩ ፕሮጀክቶች መካከል ሲሆን በተለይ የአቡዳቢ የኃይል አቅርቦት የመንግስትና የግል አጋርነት ፕሮጀክትና እንግሊዝ ሀገር የሚገኘው የሳይዝዎል ሲ የኑክሌር ፕሮጀክትን አሸንፎ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አመልክቷል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New