News

አዲስ ነገር – ችግር ፈቺ አሰራሮች

በአገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ ሰላሳ ስድስት ሆስፒታሎች ላይ ችግር ፈቺ የሆኑ አዳዲስ አሰራሮች ሊተገበሩ ነው ተባለ፡፡

ይህ የተባለው በአዲስ አበባ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች እና በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ሆስፒታሎች አራት ዋና ዋና አዳዲስ አሰራሮች እንደሚተገበሩ ይፋ በተደረገበት መድረክ ነው፡፡

በመድረኩ በየሆስፒታሎቹ የሚሰጡት አገልግሎቶች ተጠያቂነት የሰፈነባቸው፣ መረጃዎችን መሰረት ያደረጉ፣ ለተገልጋይ ቅድሚያ የሚሰጡ፣ አስተማማኝና ውጤታማ እንዲሆኑ ይረዳሉ የተባለ ሲሆን እንዲሁም በየተቋማቱ ያለውን የሰውና የቁሳቁስ ሃብቶችን በአግባቡ በመጠቀም ቅንጅታዊ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ በተገልጋይና በባለሙያዎች በኩል ለሚነሱ ቅሬታዎች መፍትሄ የሚያስገኙ ይሆናሉ ተብሏል።

በድንገተኛ፣ በተኝቶና በተመላላሽ ህክምና፣ በመድሃኒት አቅርቦት፣ በላብራቶሪ እና በኢሜጂንግ አገልግሎት እንዲሁም በሌሎች ክፍሎች ላይም አራቱ አንኳር ተግባራት ተግባራዊ እንደሚደረጉ የተጠቆመ ሲሆን ሆስፒታሎቹ ለተገልጋይ በሚሰጡት አገልግሎት እንደሚመዘኑና የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሆስፒታሎችም እውቅና በመስጠት እንደሚበረታቱ ተገልጿል መባሉን ከጤና ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተመልክተናል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New