አዲስ ነገር – ድጋፍ ለጌርጌሴኖን በ6860
ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከልን ህብረተሰቡ ድጋፍ ማድረግ የሚችልበትን አጭር የመልዕክት መቀበያ ቁጥር ይፋ አደረገ።
ህብረተሰቡ 6860 ኦኬ በማለት ብቻ ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስችለው የተገለጸው ይህ አገልግሎት በኢትዮ ቴሌኮም አማካኝነት የቀረበ መሆኑ አዲስ የሚያስገነባውን ህንፃ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ ሰምተናል።
ማዕከሉ አሁን ላይ ከ500 በላይ የአእምሮ ህሙማንን ከጎዳናና በማንሳት በኪራይ ቤት አስገላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ማዕከሉ አሁን ላይ በሚገኝበት የኪራይ ቤት ውስጥም በቂ ምግብ ማብሰያ ባለመኖሩ ህሙማኑን ለመርዳት እየተቸገረ መሆኑን በመግለጽ ህብረተሰቡ ለህንፃው ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃና ማገገሚያ ማዕከል ከተመሰረተበት 1998 ዓ.ም ጀምሮ ለ16 ዓመታት ያህል በርካታ የአዕምሮ ሕሙማንና በተለያየ በሽታዎች የሚሰቃዩ አንስቶ በመንከባከብ ላይ ይገኛል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New