News

አዲስ ነገር – የኢትዮጵያ አልጄሪያ ወዳጅነት

የኢትዮጵያና የአልጄሪያን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የአልጄሪያ ኢትዮጵያ ወዳጅነት ቡድን መመስረቱ ተነገረ፡፡
የወዳጅነት ቡድን ምሥረታውን ምክንያት በማድረግ በአልጄሪያ ብሔራዊ ፓርላማ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ ኢትዮጵያና አልጄሪያ በፖለቲካ መስክ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሃገራት መሆናቸው የተነሳ ሲሆን ይህንን ግንኙነትም በፓርላሜንታዊ ዲፕሎማሲ በማጎልበት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ በኩልም በአልጄሪያ ፓርላማ የአልጄሪያ ኢትዮጵያ ወዳጅነት ቡድን መመሥረት የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው የተባለ ሲሆን የፓርላማ ለፓርላማ ግንኙነቱ መጠናከር በሁለቱ ህዝቦች መካከል ከፖለቲካው ባሻገር የህዝብ ለህዝብ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር አመቺ ዕድል እንደሚፈጥርም ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New