News

አዲስ ነገር – የኩላሊት ህክምና ማዕከል

በመንግስትና በግል ትብብር የተገነባው የኩላሊት ንቅለ ተከላና እጥበት ማዕከል ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ተመርቆ ስራ መጀመሩ ተነግሯል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስት ጽ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ያሰረፈረው መረጃ እንደሚያሳየው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በየአብ የህክምና ማዕከል በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የተገነባው ማዕከሉ 90 ታካሚዎችን የመቀበል አቅም አለው፡፡
በኩላሊት እጥበት አገልግሎት አሰጣጥ አለምአቀፍ ደረጃዎችን ያሟላ ነው የተባለው ማዕከሉ በተለይ ዝቅተኛ እና ምንም ገቢ ለሌላቸው የህበረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት መስጠት ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምርቃት ስነስርኣቱ ላይ ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ሁለት አመታት ለኩላሊት እጥበት ህክምና 24 ሚሊዮን ብር ድጎማ ማድርጉን ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባን የጤና ማዕከል ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ 24 ቦታዎችን ለግሉ ዘርፍ የሰጠ መሆኑንና በራሱ አቅም ደግሞ ሶስት ሆስፒታሎችን በጀት መድቦ እየገነባ ስለመሆኑ ከንቲባዋ አስታውቀዋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New