EthiopiaNews

ኢትዮጵያ እና አይ ኤም ኤፍ

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተሯ ጋር በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

አይ ኤም ኤፍ ከአንድ ወር በፊት ባወጣው የኢኮኖሚ ትንበያው በፈረንጆቹ 2026 አመት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት በ9.2 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ሲል መተንበዩ የሚታወስ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ የ10.2 በመቶ እድገት ታስመዘግባለች ብለው መናገራቸው ይታወሳል።

መረጃው ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ይፋዊ የማኅበራዊ ገፅ የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv